
አዲስ አበባ: ታኅሣሥ 22/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ሚኒስትሩ አሚኮ በቅርቡ የሚያስመርቀውን የአዲስ አበባ ዘመናዊ ስቱዲዮን ከመንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች ጋር ጎብኝተዋል። አሚኮ ባለፉት 30 ዓመታት የድርጅታዊ እድገቱ የሚጨበጥ ትልቅ ለውጥ የመጣበት ነው ብለዋል።
ከቆርቆሮ በቆርቆሮ የሥራ ቦታ ተነስቶ አሁን እስካለበት የትልልቅ ስቱዲዮ፣ የብዙ ራዲዮ ጣቢያዎች፣ የዲጅታል ሚዲያ አቅም እና ከ11 በላይ ቋንቋዎችን የሚናገር ድርጅት ለመኾን በቅቷል ብለዋል። አሚኮ በሀገሪቱ ተወዳዳሪ ሚዲያ ኾኗል ስንል በብራንድ ግንባታ የሚታይ አቅም መፍጠር መቻሉ መኾኑን መጥቀስ ከበኩር እስከ አሚኮ የደረሰ የብራንድ አቅም ያለው ነው ብለዋል።
በትርክት ግንባታ እና በማኅበረሰብ ትስስር ከክልሉ አልፎ ለሀገሪቱም ትልቅ ሚና እየተወጣ ያለ ድርጅት ነው ብለዋል። አሚኮ በስያሜ ደረጃ የክልል ስያሜ ይያዝ እንጂ “የኢትዮጵያ ሚዲያ ኮርፖሬሽን” መኾኑን በሚያሳይ ደረጃ እየሠራ ያለ ነው ብለዋል። በመኾኑም አሚኮ ቀድሞ የክልሉን አካታችነት በሚያሳይ መልኩ ለብዝኀነት ግንባታ ቅድሚያ ሰጥቶ የሚሠራ በመኾኑ ሀገሪቱ ለምትፈልገው የጋራ ሀገራዊ ግብ መዳረሻ የኾኑ ሥራዎችን እየሠራ ነው ብለዋል።
አሚኮ በ11 ቋንቋዎች ሲያሰራጭ ከጋራ ትርክት ግንባታ ባለፈ የሌሎቹን ቋንቋ ባሕል እና እውቀትም ከማክበር የሚመነጭ ነው ብለዋል። አሚኮ ወደፊት መዳረሻውን ቀጣናዊ እና አሕጉራዊ ራዕይ ይዞ መሥራት አለበት ሲሉ ያሳሰቡት አቶ መላኩ ያን ማከናወን የሚያስችል ተቋማዊ ተሞክሮው ጥሩ መኾኑን አንስተዋል።
አሚኮ ለሰላም ቅድሚያ ሰጥቶ መሥራት እንደሚገባው በማንሳት የተረጋጋ አካባቢ እንዲፈጠር እና የተሳካ ማኅበራዊ ኑሮን ማስቀጠል በሚያስችል መልኩ መሥራት ይገባዋል ሲሉ አሳስበዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!