የአማራ ክልል ምክር ቤት በረቂቅ አዋጆች ዙሪያ ከሕዝብ ወኪሎች ጋር እየተወያየ ነው።

108

ባሕር ዳር: ታኅሣሥ 22/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ምክር ቤት ረቂቅ አዋጆችን ሕግ ኾነው ከመጽደቃቸው በፊት ለሕዝብ ወኪሎች አቅርቦ በሕዝብ ሰሚ መድረክ ውይይት እያደረገ ነው።

ረቂቅ ሕጎቹ፦
👉የአብክመ የአሥተዳደር ሥነ ሥርዓት ረቂቅ አዋጅ፣
👉 የአብክመ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ረቂቅ አዋጅ፣
👉 የአብክመ የጥብቅና ፈቃድ አሰጣጥ እና አሥተዳደር ረቂቅ አዋጅ
👉 የአብክመ ማረሚያ ቤቶች ረቂቅ አዋጅ ናቸው።

በሕዝብ ሰሚ መድረኩ የሕዝብ ምክር ቤቶች ተወካዮች፣ የሕግ ባለሙያዎች፣ የሲቪክ ማኅበረሰብ ድርጅቶች እና የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል። በረቂቅ ሕጎቹ ላይ ማብራሪያ ከቀረበ በኋላ ከሕዝብ የተወከሉ ተሳታፊዎች አስተያየት እንደሚሰጡባቸው ይጠበቃል።

ተቋማት የአሠራር መመሪያ በማውጣት አገልግሎት እንዲያቀላጥፉ እና በ’መመሪያ አልወጣለትም’ ምክንያት ተገልጋዮች እንዳይጉላሉ እንደሚያስችልም በውይይቱ ተነስቷል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየአማራ ክልል ውኃና ኢነርጂ ቢሮ የንጹህ መጠጥ ውኃን ለማሳደግ እየሠራ ነው።
Next articleአሚኮ በይዘት ቀረጻ ሥርፀት የራሱን መለያ መፍጠር የቻለ የሚዲያ ተቋም መኾኑን የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ መላኩ አለበል ተናገሩ።