በም/ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኀላፊና የብልጽግና ፓርቲ ም/ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ መልእክት፦

48

ፓርቲያችን ብልፅግና ትላንት የስርዓተ መንግስት አስተዳደራችን አንድ አካል ሆነው ካለፉ ልንቀይራቸው ከማንችላቸው ታሪኮች ጋር ፈፅሞ ፀብ የለውም።

በመርህ ደረጃ ከትላንት ተምሮ፣ዛሬን አሳምሮ፣ነገን የተሻለ ማድረግን በማመን የበለፀገች ኢትዮጵያን ለመፍጠር በመትጋት ላይ ይገኛል።

የብሔራዊ ቤተመንግስት እድሳት አቧራን አራግፎ አሻራን የማኖር ስራም በዚሁ እሳቤ የተቃኘ ነው።

ጥበብ እና ኢትዮጵያ፤ ስልጣኔ እና ኢትዮጵያ፤ ኅብረ-ብሔራዊነት እና ኢትዮጵያ፤ ቀደምትነት እና ኢትዮጵያ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታ የሆኑ በልኳ ተሰፍተው ስሟ ሲጠራ አብረው የሚነሱ ተቀፅላዎቿ መሆናቸውን በስፍራው የተሰደረው መኪናውም፣የንግስና ካባውም፣ ዙፋኑም እና የተለያዩ የሀገራችንን አከባቢዎች የሚገልፁ ስጦታዎችና ሌሎች መገለጫዎች ይመሰክራል።

ትላንት ታሪክ ነው! ዛሬ ቅርስ ነው! ነገ ውርስ ነውና እይታችንን ልዕልና መር ጉዞ ላይ በማድረግ ለሁላችንም የምትሆን ኢትዮጵያን ለመፍጠር እንትጋ!!

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበበዓል ምክንያት ወደ ላሊበላ እና ጎንደር ከተማ የሚያደርገውን በረራ እንደሚያሳድግ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ገለጸ።
Next articleየመፍትሄዎች ሁሉ መንገድ!