
ገንዳ ውኃ: ታኅሣሥ 22/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በምዕራብ ጎንደር ዞን በገንዳ ውኃ ከተማ አሥተዳደር በቤት ውስጥ ተደብቆ የነበረን ሥምንት ኩንታል አደንዛዥ እጽ በማኅበረሰቡ ጥቆማና በጸጥታ ኃይሎች መያዙን የገንዳ ውኃ ከተማ አሥተዳደር ፖሊስ ጽሕፈት ቤት አስታውቋል።
የገንዳ ውኃ ከተማ አሥተዳደር ፖሊስ ጽሕፈት ቤት ተወካይ ኀላፊ ኢንስፔክተር ኃይሌ ብርሃኑ እንደተናገሩት ማኅበረሰቡ ባደረገው መልካም ትብብር እና ጥቆማ መሠረት አደንዛዥ እጹ ወደማኅበረሰቡ ሊሰራጭ በታሰበበት ሰዓት ነው የተያዘው።
ልዩ ቦታው በከተማው ቀበሌ 01 በተለምዶ አዎዬ ሠፈር ተብሎ በሚጠራው ቦታ ቤት ውስጥ ተደብቆ እንደተያዘም ለአሚኮ አስረድተዋል።
የተያዘው ሰባቱ ኩንታል አደንዛዥ እጽ እና አንድ ኩንታል የአደንዛዥ እጽ ዘር መኾኑንም ጠቁመዋል።
ኢንስፔክተሩ ማኅበረሰቡ ላደረገው ትብብር አመስግነው ቀጣይም እንዲህ ዓይነት ወንጀል ሲያጋጥም ጥቆማ እንዲሰጡ መልዕክት አስተላልፈዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!