“እጅን በመታጠብ ብቻ 20 በመቶ የሚኾኑ በሽታዎችን መከላከል ይቻላል” አቶ አብዱልከሪም መንግሥቱ

36

ባሕር ዳር: ታኅሣሥ 22/2017 ዓ.ም (አሚኮ) “ንጹሕ እጆች ለጤናችን ዋስትና ናቸው” በሚል መሪ መልእክት የእጅ መታጠብ ቀን በባሕር ዳር ከተማ እየተከበረ ነው።

በክብረ በዓሉ ላይ የተገኙት የአማራ ክልል ጤና ቢሮ ኀላፊ አብዱልከሪም መንግሥቱ የንጽሕና አጠባበቅን በተመለከተ እንደክልል በትኩረት እየተሠራ ይገኛል ብለዋል።

“እጅ በመታጠብ ብቻ 20 በመቶ የሚኾኑ በሽታዎችን መከላከል ይቻላል” በማለት ገልጸዋል ቢሮ ኀላፊው።

እጅን በአግባቡ በመታጠብ ትራኮማ በሽታን ለመቆጣጠር ይቻላል ያሉት ቢሮ ኀላፊው ማኅበረሰቡ ከሳሙና እና ውኃ በተጨማሪ ሌሎች አማራጮችን ተጠቅሞ እጅን መታጠብ ይገባል ነው ያሉት።

ሁሉም ማኅበረሰብ በየደረጃው መፀዳጃ ቤቶችን ገንብቶ እንዲጠቀም በማስቻል ረገድ የሁሉም ኀላፊነት ሊሆን እንደሚገባ ቢሮ ኀላፊው አሳስበዋል። የእጅ መታጠብ ቀን በዓለም ለ16ኛ በኢትዮጵያ ደግም ለ15ኛ ጊዜ እየተከበረ ይገኛል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleስለአራጣ የወንጀል ሕጉ ምን ይላል?
Next articleበቤት ውስጥ ተደብቆ የነበረን አደንዛዥ ዕጽ መያዙን የገንዳ ውኃ ከተማ አሥተዳደር ፖሊስ ጽሕፈት ቤት አስታወቀ።