
አዲስ አበባ: ታኅሣሥ 21/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የርእሰ መሥተዳድሩ የሕዝብ ግንኙነት አማካሪና የአሚኮ የቦርድ ሰብሳቢ ይርጋ ሲሳይ አሚኮ በአዲስ አበባ ያስገነባውን ዘመናዊ ስቱዲዮ ከክልሉ እና ከሀገሪቱ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር በመኾን ተመልክተዋል።
የቦርድ ሰብሳቢው በዚህ ወቅት ባስተላለፉት መልእክት አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን በ30 ዓመታት ጉዞው በተለያዩ የእድገት ደረጃዎች አልፎ ዛሬ ጠንካራ እና ተወዳዳሪ ተቋም ለመሆን በቅቷል ብለዋል። የሚዲያ ተቋሙ ለሚፈለገው የሰላም እና የዲሞክራሲ ግንባታ በአሁኑ ወቅት ያለው ሚና ትልቅ መሆኑን በአግባቡ በመረዳት እየሠራ መኾኑንም ገልጸዋል።
አሚኮ ከዚህ በላይ ጠንካራ እና ተዕፅኖ ፈጣሪ ሚዲያ እንዲኾን ድጋፍ ማድረግ ያስፈልጋል ነው ያሉት። የፖሊሲ እና የመመሪያ ማሻሻያዎች እያደረገ ዘመኑን በሚመጥን ሁኔታ እንዲራመድ አሚኮ ሁለገብ ድጋፍ እንደሚያስፈልገውም አብራርተዋል።
ብዝኀነትን በማረጋገጥ ደረጃ አሚኮ ግንባር ቀደም ነው ያሉት አቶ ይርጋ ዛሬ ሳይሆን ትናንት በአግባቡ ለብዝኀ ዲሞክራሲ ግንባታ የበኩሉን እየተወጣ መዝለቁን አስታውሰዋል። ይህ ትልቅ ተግባሩም ዛሬ ለምንፈልገው የጋራ ገዥ ትርክት ግንባታ በቂ ርሾ ያለው የሚዲያ ተቋም ኾኖ እንዲገኝ አስችሎታል ነው ያሉት።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!