
አዲስ አበባ ፡ ታኅሣሥ 21/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ርእሰ መሥተዳድሩ ይህን ያሉት አሚኮ በአዲስ አበባ ያስገነባውን ስቱዲዮ ከክልሉ እና ከሀገሪቱ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር በጎበኙበት ወቅት ነው። “የአሚኮ ስቱዲዮ ምልከታ በማድረጋችን ደስተኞች ነን” ብለዋል ርእሰ መሥተዳድሩ።
አንድ ተቋም እንደተቋም ግንባታውን ለማስቀጠል የሰው ኃይል ግንባታ መጎልበት ይገባዋል ብለው ይህንን ለማጠናከር አሚኮ ለባለሙያዎቹ ክህሎትን እና ተልዕኮውን በአግባቡ እንዲወጡ የሚያስችል ሥልጠናዎችን እየሰጠ መሆኑንም ገልጸዋል።
አሚኮ ሁሌም እንደሚለው ለኅብረተሰብ ለውጥ በመትጋት ኅብረተሰብ ለመጥቀም በሚያስችለው አግባብ ሥራ ላይ መሆኑንም ርእሰ መሥተዳድሩ ጠቅሰዋል።
“ከዚህ ባለፈ የኢትዮጵያውያንን ቋንቋ በመናገር የክልሉን ብቻ ሳይሆን የሀገር አቅምነቱን እያስመሰከረ ነው፤ ይህ ተግባር ለጋራ ገዥ ትርክት ግንባታ ሚናው የላቀ ነው” ብለዋል።
አሚኮ የምንኮራበት በክልሉ ማንነት ብቻ ሳይሆን በቀጣናው ተዕፅኖ ለመፍጠር እየተጋ የሚገኝ የሚዲያ ተቋም መኾኑንም ርእሰ መሥተዳድሩ አስገንዝበዋል።
አሚኮ በዚህ ትጋት ውስጥ ለመኖሩ አስተዋፅኦ ለሚያደርጉ የሚዲያው አመራሮች እና ባለሙያዎች አቶ አረጋ ምሥጋና አቅርበዋል።
አሚኮ ለክልሉ ሰላምና ልማት መረጋገጥ ከፍተኛ ኃላፊነት ያለበት በመሆኑ ሥራውን አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባውም አሳስበዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!