
አዲስ አበባ: ታኅሣሥ 21/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ይህንን ያሉት አሚኮ በአዲስ አበባ ያስገነባውን ዘመናዊ ስቱዲዮ ዛሬ ሲጎበኙ ባስተላለፉት መልዕክት ነው። አሚኮ ቀደምት ከምንላቸው ተቋማት አንዱ ነው ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተቋሙ ከአነስተኛ የሥራ ክፍሎች ወጥቶ በሚያምር እና ትልቅ ስቱዲዮ በመድረሱ ደስተኛ ነኝ ብለዋል። ሚዲያው በየደረጃው እየተለወጠ ከዚህ እንዲደርስ ላደረጉ ሁሉ ምስጋናም አቅርበዋል።
የሚዲያ ውድድሩ እያደገ በመሆኑ ከዘመኑ ጋር የሚራመድ አሠራርን መከተል እንደሚገባም አስገንዝበዋል። አሚኮ ይህንን ሲገነባ በሰው ኃይልም ብቁ ባለሙያዎችን ማፍራት እንደሚያስፈልግም ገልጸዋል። የሥራ ኀላፊዎች ሚዲያን ሊጠቀሙበት እንደሚገባም አሳስበዋል። መንግሥትም ሚዲያው ውጤታማ እንዲሆን እንደሚደግፍ ተናግረዋል።
አሚኮ ቀደም ብሎም በቅርበት ስናውቀው ታታሪ ጋዜጠኞች እና ባለሙያዎች 24 ሰዓትና ሰባት ቀናትን በመሥራት የሚተጉ ባለሙያዎችና አመራሮች ያሉበት መሆኑን በተግባር ያየነው ስለሆነ ይህ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ነው ያሉት።
በአንዷለም መናን
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!