አሚኮ ገዥ ትርክት በመፍጠር ለሀገር ግንባታ ወሳኝ ሚና እየተጫወተ መሆኑን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመሥገን ጥሩነህ ገለጹ።

24

ባሕር ዳር፡ ታኅሣሥ 21/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመሥገን ጥሩነህ ከአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ እና ከሌሎች የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ መሪዎች ጋር በመሆን የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን – አሚኮ በአዲስ አበባ የገነባውንና ዘመኑ የደረሰበትን የሚዲያ ቴክኖሎጂ ያሟላውን ዘመናዊ ስቱዲዮ ዛሬ መጎብኘታቸውን ገልጸዋል።

አሚኮ የገነባቸው የሬዲዮና የቴሌቪዥን ስቱዲዮዎች መንግሥት ለጠንካራ ሚዲያ ግንባታ የሰጠውን ትኩረት ማሳያ መሆናቸውን በማኅበራዊ ገጻቸው ባስተላለፉት መልእክት አስታውቀዋል፡፡ ሚዲያው ለኅብረተሰብ ለውጥ በመትጋት፣ የመንግሥትን ሥራዎች ለሕዝብ በማድረስና ገዥ ትርክት በመፍጠር ለሀገር ግንባታ ወሳኝ ሚና እየተጫወተ ነው ብለዋል።

አሁን ያለንበት ዘመን እያንዳንዱ ግለሰብ በያዘው ዲጂታል መሣሪያ፣ መረጃ ያለ ገደብ የሚያሠራጭበት ነው፡፡ በመሆኑ የሀገራችን ሚዲያዎች ይህንን ታሳቢ ያደረገ የይዘት ጥራት፣ ፍጥነትና ተደራሽነት ላይ በስፋት መሥራት ይጠበቅባቸዋል ነው ያሉት። እንደ ሀገር የጀመርነውን ሁለንተናዊ ሪፎርም በትጋት፣ ፍጥነት እና ጥራት ለመፈፀም ሚዲያዎች ጉልህ ሚና እንዲጫወቱ ለማስቻል መንግሥት አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleከስምንት ሚሊዮን ኩንታል በላይ ማዳበሪያ ለማቅረብ እየሠራ መኾኑን የአማራ ክልል ግብርና ቢሮአስታወቀ።
Next article“አሚኮ 24 ሰዓትና ሰባት ቀናትን የሚተጉ ባለሙያዎች ባለቤት በመሆኑ ይህ ሚዲያው አሁን ለደረሰበት እድገት አስተዋፅኦው ከፍተኛ ነው” ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ