በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የተመራ የኢትዮጵያ ልዑክ በዶራሌ ሁለገብ ወደብ ተገኝቶ የ2017/18 የአፈር ማዳበሪያ ኦፕሬሽን ውይይት አደረገ።

47

ባሕር ዳር: ታኅሳስ 21/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ.ር) የተመራ የኢትዮጵያ ልዑክ የዶራሌ ሁለገብ ወደብ እና ተርሚናልን ጎብኝቷል።

ልዑኩ በወደቡ ያለውን አጠቃላይ የገቢ እና ወጪ ምርት ሂደት ተመልክቷል።

የልዑካን ቡድኑ አባላት በጉብኝቱ ወቅት ከወደቡ የሥራ ኀላፊዎች ጋር የ2017/18 የአፈር ማዳበሪያ ኦፕሬሽን አስመልክቶ ውይይት ማድረጋቸውን በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመለክታል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleለሽግግር ፍትሕ ስኬታማነት ሁሉም አካል ድርሻ አለው” የአማራ ክልል ፍትሕ ቢሮ
Next article“ሕዝቡ ልጆቼ እንዳይማሩ የሚከለክል ሁሉ ጠላቴ ነው ሊል ይገባል” ሙሉነሽ ደሴ (ዶ.ር)