
ባሕር ዳር: ታኅሣሥ 18/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ሰላም እና ፀጥታ ቢሮ ከጎንደር ቀጠና የፀጥታ መዋቅር ጋር ወቅታዊ የሕግ ማስከበር ሥራዎችን ገምግሟል። የቀጣይ መሰረታዊ የሕግ ማስከበር ሥራዎች ላይም ውይይት ተደርጎ አቅጣጫ ተቀምጧል።
ከተራ እና የጥምቀት የሕዝብ ሰላም እና የበዓላቱ ሥርዓት ተጠብቆ እንዲከበሩ በሚቻልበት ኹኔታ ላይም ምክክር ተደርጓል። በዓላቱን ተከትሎ ሕዝብን ሰላም ለመንሳት መንሳት የሚንቀሳቀሱ አካላት እንዳይኖሩ ከወዲኹ እየተሠራ ስለመኾኑም በውይይቱ ተነስቷል።
ከመላ ሕዝቡ ጋር በመኾን አስፈላጊ የቅድመ ዝግጅት ተግባራት እየተከናወኑ ሥለመኾኑም ተነግሯል። ከወጣቶች ጋር በመኾን ለበዓላቱ ራሱን የቻለ እቅድ ተዘጋጅቶ በሥርዓት እንዲመራም አቅጣጫ ተቀምጧል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!