ሀገር በቅብብሎሽ የምትቀጥል እንደመኾኗ ለተተኪ ተውልድ ትኩረት መስጠት ያስፈልጋል።

36

እንጅባራ: ታኅሣሥ 18/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የአዊ ብሔረሰብ አሥተዳደር የሕጻናት ፓርላማ ሦስተኛ ዙር መሥራች ጉባዔ በእንጅባራ ከተማ ተካሂዷል። በጉባዔው የወረዳዎች እና ከተማ አሥተዳደሮች የሕጻናት ፓርላማ አፈ ጉባዔዎች፣ የአዊ ብሔረሰብ ምክር ቤት አፈ ጉባዔዎች፣ የቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢዎች እና ሌሎች ባለ ድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።

የአዊ ብሔረሰብ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባዔ ሙሉዓዳም እጅጉ የሕጻናት ፓርማ ሕፃናት በሀገራቸው የልማት እና የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ተሳትፏቸውን የሚያጎለብቱበት፣ የዴሞክራሲ መርሕ እና ሥርዓት የሚላመዱበት እንደሆነ ተናግረዋል። “ሀገር በቅብብሎሽ የምትቀጥል እንደመኾኗ ለተተኪ ተውልድ ትኩረት መስጠት ያስፈልጋል” ነው ያሉት።

የአዊ ብሔረሰብ አሥተዳደር ሴቶች ሕጻናት እና ማኅበራዊ ጉዳይ መምሪያ ኀላፊ አምባነሽ ስሜነህ በብሔረሰብ አሥተዳደሩ የሕጻናት ፓርላማ ከተቋቋመ ከ2010 ዓ.ም ወዲህ ሕጻናት ትኩረት እንዲሰጣቸው እና ሀሳባቸው እንዲደመጥ በር እየከፈተ መኾኑን ተናግረዋል።

በብሔረሰብ አሥተዳደሩ አንዳንድ አካባቢዎች የሚስተዋሉ ያለ ዕድሜ ጋብቻ፣ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች እና በሕጻናት ላይ የሚደርስ የጉልበት ብዝበዛን በማስቀረት ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ እንደኾነም ኀላፊዋ ገልጸዋል።

ተመራጭ የፓርላማ አባላትም የሕጻናት መብት እና ጥቅሞች እንዲከበሩ ከሌሎች ባለ ድርሻ አካላት ጋር በመኾን እንደሚሠሩ ተናግረዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበጎ ፈቃደኞች ለኢትዮጵያ የአፍሪካ የዲፕሎማሲ ማዕከልነት እየተወጡት ያለው ሚና የሚደነቅ መኾኑን ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ.ር) ገለጹ።
Next articleተፈናቃዮችን በዛላቂነት ለማቋቋም ኹሉም አካል ርብርብ እንዲያደርግ ተጠየቀ።