ተፈናቃዮችን በዛላቂነት ለማቋቋም የሚያግዝ ስትራቴጂ ሰነድ ላይ ምክክር እየተካሄደ ነው።

40

ባሕር ዳር: ታኅሣሥ 18/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በክልሉ ከሰው ሠራሽ እና ከተፈጥሮ አደጋዎች ጋር በተያያዘ ለተፈናቀሉ ዜጎች ዘላቂ መፍትሄ በመስጠት እና በማቋቋም ዙሪያ ከአጋር አካላት ጋር ውይይት መካሄድ ጀምሯል።

ከዩ ኤን ዲ ፒ እና ከአማራ ክልል የአደጋ መከላከል እና ምግብ ዋስትና ኮሚሽን ባለሙያዎች የተውጣጣ የጥናት ቡድን ተደራጅቶ የስትራቴጂ ሰነድ እና የሚጠይቀውን የድጋፍ ልክ ለማወቅ እና ለተፈናቃዮች ዘላቂ መፍትሄ ለመስጠት ሢሠራ ቆይቷል፡፡

በተያዘው ዓመት ጥቅምት ወር በስትራቴጂ ሰነዱ ላይ ዐውደ ጥናት ተካሂዶ ግብዓት ተወስዶበታል። ዛሬም ለሁለተኛ ጊዜ ከእርዳታ ሰጭ ድርጅቶች ጋር ምክክር የተደረገ ሲኾን ይህም ሃሳባቸውን እንዲገልጹ እና ተጨማሪ ግብዓት እንዲሰጡ የሚያግዝ መኾኑ ተገልጿል፡፡

በአጋርነት ለሚሠሩ ሴክተሮች እና ለሚመለከታቸው አካላት የስትራቴጂ ሰነዱ ቀርቦ ውይይት እየተደረገም ይገኛል፡፡ በመድረኩ የክልሉ ኮሙንኬሽን ቢሮ ኀላፊ መንገሻ ፈንታው (ዶ.ር)፣ የክልሉ አደጋ መከላከል እና ምግብ ዋስትና ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር እታገኘሁ አደመን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች፣ ጉዳዩ የሚመለከታቸው አጋር አካላት ተወካዮች እና ተጋባዥ እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ሀገራዊ ምክክሩ በወሳኝ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ተግባብተን እንድናልፍ የሚያደርግ ነው” ዶክተር ደሴ ጥላሁን
Next articleየቅጥር ማስታወቂያ !