ከ60 ሺህ በላይ ወገኖችን የማኅበረሰብ አቀፍ ጤና መድኅን ተጠቃሚ ለማድረግ ማቀዱን የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር አስታወቀ።

17

ባሕር ዳር: ታኅሣሥ 17/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ከ60 ሺህ በላይ ወገኖችን የማኅበረሰብ አቀፍ ጤና መድኅን ተጠቃሚ ለማድረግ ማቀዱን የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ጤና መምሪያ አስታውቋል። የባሕርዳር ከተማ አሥተዳደር ጤና መምሪያ የ2017 ዓ.ም የጤና መድኅን የነባር አባላትን እድሳት እና የአዲስ አባላት ምዝገባ ንቅናቄ መድረክ አስጀምሯል።

ንቅናቄው ” እንደ አቅሜ አዋጣለሁ፤ እንደ ሕመሜ እታከማለሁ” በሚል መሪ መልእክት ነው የተጀመረው። የማኅበረሰብ አቀፍ ጤና መድኅን ንቅናቄው እስከ ጥር 30 2017 ዓ.ም ይቆያል ተብሏል። የባሕርዳር ከተማ አሥተዳደር ጤና መምሪያ ኃላፊ ዓለም አሰፋ በ2016 ዓ.ም ከ58 ሚሊዮን ብር በላይ ለሕክምና ወጭ እንዲውል ተደርጓል ብለዋል። ለአንድ አባልም እስከ 133 ሺህ ብር ድረስ ወጭ ኾኗል ነው ያሉት።

በ2017 ዓ.ም ከ63 ሺህ በላይ የኅብረተሰብ ክፍሎችን የማኅበረሰብ አቀፍ ጤና መድኅን ተጠቃሚ ለማድረግ ታቀዶ እየተሠራ መኾኑን ተናግረዋል። የባሕርዳር ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ጎሹ እንዳላማው የጤና መድኅን በራሳቸው አቅም ለመታከም የገንዘብ እጥረት ላለባቸው ወገኖች በጋራ ክፍያ (መዋጮ) እንዲታከሙ በማድረግ የበርካታ ወገኖችን እንግልት ቀንሷል ብለዋል። የእርስ በእርስ የመደጋገፍ ባሕልንም እያጠናከረ የመጣ ነው ብለዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleተፈናቃዮች ወደቀያቸው ተመልሰው ሰላማዊ ኑሮ እንዲመሩ ለማድረግ መንግሥት ቁርጠኛ መኾኑ ተገለጸ፡፡
Next article“ብልጽግና ከተሞች ለነዋሪዎች ምቹ እንዲኾኑ እየሠራ ነው” አዳነች አቤቤ