
አዲስ አበባ: ታኅሣሥ 17/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ባለፉት አምስት ወራት 380 ቢሊየን ብር ገቢ መሰብሰቡን የገቢዎች ሚኒስትር ዓይናለም ንጉሴ ገለጸዋል። ባለፉት 5 አመታት እንደሀገር መሰረታዊ ለውጦችን በማካሄድ በርካት የልማት ሥራዎች መሰራታቸዉን የገቢዎች ሚኒስትሯ አይናለም ንጉሴ ተናግረዋል።
ተቋሙ በ13 ቅርጫፍ ጽሕፈት ቤቶች በአዲስ ሪፎርም ገቢ በመሰብሰብ ላይ እንደሚገኝም ተናግረዋል። ባለፉት አምስት አመታት በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ፈተና የኾነውን ኮንትሮባንድ ለመከላከል አዲስ ሪፎርሞች መካሄዳቸው በገቢ አሰበሳሰብ ላይ ለውጥ እንዲመጣ ትልቅ አስተዋጽኦ ማድረጉን ሚኒስትሯ ተናግረዋል።
እንደ ሀገር የኢኮኖሚ ማሻሻያውን ሊደግፍ የሚችል እና አስተማማኝ የፋይናንስ ምንጭ እንዲኖር የገቢ አሰባሰብ ሂደት ላይ በትኩረት እየተሰራ ነው ብለዋል በአንዳንድ ክልሎች የሚስተዋለው የሰላም እጦት የታክስ አሰባበቡ እንዲቀንስ በማድረግ ላይ ነው ያሉት ሚኒስትሯ በቀጣይም የገቢ እድገቱ የተፋጠነ እንዲሆን ሁሉም በትብብር ለሰላም ዘብ ሊቆም ይገባል ብለዋል።
አሁን ላይ በአምስት ወር ብቻ 380 ቢሊየን ብር ገቢ መሰብሰቡን ተናግረዋል።
ዘጋቢ:- ራሔል ደምሰው
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!