“የኢትዮጵያ ገበያ በሚፈልገው መንገድ የተቃኜው የክህሎት ልማት ሥራ ለውጥ አምጥቷል” ሙፈሪያት ካሚል

32

አዲስ አበባ: ታኅሣሥ 17/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አሥፈፃሚ እና የሥራ እና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪያት ካሚል ሥነ ምህዳሩን ለሥራ ፈጣሪዎች ምቹ ማድረግ ኢትዮጵያ ያላትን እምቅ አቅም እና ፀጋ በአግባቡ መጠቀም እንድትችል በር ከፋች ነው ብለዋል። የሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ከመመሥረቱ አስቀድሞ ለአጫጭር ሥልጠናዎች ይሰጥ የነበረው ትኩረት ዝቅተኛ እንደነበር ተናግረዋል።

የሥራ እና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪያት ከሚል ባለፉት ሦስት ዓመታት ነባር ሥርዓተ ትምህርቶችን በመከለስ እና አዳዲስ በመቅረጽ በክህሎት ልማት ሥራ አበረታች ለወጥ ተመዝግቧል ብለዋል።

የክህሎት ልማት አቅጣጫው ከአቅርቦት ወደ ፍላጎት መር መቀየሩን የሚናገሩት ሚኒስትሯ አቅጣጫው ሀገሪቱ የጀመረችውን ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ለወጥ በሚያሳካ መንገድ መቃኘት ያስፈልገዋል ነው ያሉት።

ኢትዮጵያ እየገነባችው ያለው ኢኮኖሚ ማዕከሉ ፈጠራ እንደኾነ የሚገልጹት ሚኒስትሯ ኢትዮጵያ ያላትን እምቅ አቅም መጠቀም እንዲቻል ሥነ ምህዳሩን ለሥራ ፈጣሪዎች ምቹ ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል።

ዜጎች የፈጠራ ሃሳብ እንዲኖራቸው እና ሃሳባቸውን በተግባር መንዝረው እራሳቸውንም ኾነ ሀገራቸውን እንዲጠቅሙ ቤተሰብ፣ የትምህርት ተቋማት እና መንግሥት የየድርሻቸውን ሊወጡ ይገባልም ብለዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበደሴ ከተማ የባሕል እና ኪነ ጥበብ ዓውደ ርዕይ እየተካሄ ነው።
Next article“ኢትዮጵያ ከምሥራቅ አፍሪካ ትልቁን ምጣኔ ሃብት የገነባች ሀገር ኾናለች” የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ (ዶ.ር)