በዳንግላ ወረዳ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የታጠቁ ቡድኖች መንግሥት ያቀረበውን የሰላም ጥሪ ተቀብለው ገቡ።

15

ባሕር ዳር: ታኅሣሥ 17/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በአዊ ብሔረሰብ አሥተዳደር ዳንግላ ወረዳ ጊሳ እና አካባቢው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ታጣቂ ቡድኖች ከነሙሉ ትጥቃቸው መንግሥት ያቀረበውን የሰላም ጥሪ ተቀብለው ገብተዋል፤ በዞኑ የመንግሥት የሥራ ኅላፊዎች አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

የአዊ ብሔረሰብ አሥተዳደር ዋና አሥተዳዳሪ ቴዎድሮስ እንዳለው ወደ ሠላም ከመጡ ቡድኖች ጋር በነበራቸው ቆይታ የተሰጣችሁን የሰላም ምህረት መጠቀማቸውን አድንቀው በቀጣይም ሕዝባቸውን እንዲክሱ አደራ ብለዋቸዋል። በመምጣታቸውም በብሔረሰብ አሥተዳደሩ ስም ምስጋና አቅርበውላቸዋል።

በተሳሳተ መንገድ መገዳደል ይብቃ ወደ አንድነታችን እንመለስ የሚለውን የሰላም አማራጭ በመጠቀማችሁ ሀገራችን ከሰላም እንድታተርፍ አድርጋቹሀል ብለዋል። ዋና አሥተዳዳሪው ሌሎች በጫካ ውስጥ ያሉ የቡድኑ አባላት ከጫካ ወደ ሰላም ተመልሰው ለሰላም ዘብ እንዲቆሙ ማድረግ ይጠበቅባችኋል ነው ያሉት።

በአቀባበል ሥነ ሥርዓቱ ላይ የዞኑ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች፣ የካቢኒ አባላት፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የወረዳ እና የከተማ አሥተዳደር የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበበጋ መስኖ ልማት የግብዓት አቅርቦት ችግር እንዳይኖር እየሠራ መኾኑን የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ አስታወቀ።
Next articleበደሴ ከተማ የባሕል እና ኪነ ጥበብ ዓውደ ርዕይ እየተካሄ ነው።