“ከተሜነት መጭውን ዘመን የዋጀ እንድኾን ተደርጎ እየተሠራ ነው”አሕመድን ሙሐመድ(ዶ.ር)

44

ባሕር ዳር: ታኅሣሥ 16/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የከተሞች እና መሠረተ ልማት ቢሮ፣ የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ኮሚሽን እና የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ከፍተኛ መሪዎች ጋር በመኾን እየተከናወኑ ያሉ ሥራዎችን እንደጎበኙ በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የከተማ ዘርፍ አሥተባባሪ እና የከተማ እና መሠረተ ልማት ቢሮ ኀላፊ አሕመድን ሙሐመድ(ዶ.ር) በትስስር ገጻቸው ገልጸዋል።

የሰላም፣ የልማት እና የመልካም አሥተዳደር ሥራዎች ዙሪያ ውይይት እንዳደረጉም ገልጸዋል። የዲጂታል፣ የኮሊደር ልማት እና የህጻናት ማዕከል ጉብኝት መደረጉንም አንስተዋል። በዲጂታይዜሽን፣ በአገልግሎት ዘርፍ፣ በኢንቨስትመንት፣ በኮሊደር ልማት፣ ኢትዮኮደርስ፣ የሌማት ቱርፋት እና የቀዳማይ ልጅነት ላይ በከተማችን ዘርፈ ብዙ ሥራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ።

በፌደራል መንግሥት ተቋማት እና በክልል መንግሥት ድጋፍ እንዲሁም በከተማ አሥተዳደሩ በኩል ኅብረተሰቡን በማሳተፍ እየተካሄዱ ያሉ ሥራዎች አበረታች ናቸው ብለዋል። በከተሞቻችን ሁሉን ዓቀፍ የተቀናጀ እና አካታች የከተማ ልማት ሥራዎች ተጠናክረው ቀጥለዋል ነው ያሉት።

የክልላችን መዲና ባሕር ዳርም ለነዋሪዎቿ እና ለጎብኝዎቿ ምቹ እና አስተማማኝ እንድትኾን እንዲሁም ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲረጋገጥ የተጀመሩ አበረታች ሥራዎችን ክትትል እና ድጋፍ የምናደርግበትን አሠራር አጠናክረን የምንቀጥል ይሆናል ብለዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ብልጽግና ፓርቲ ለሕዝብ ቃል በገባው መሰረት በዘላቂ ሰላም ግንባታና አካታች ልማት ስኬቶችን አስመዝግቧል” ተመሥገን ጥሩነህ
Next article”ሙስና እየከፋ ሄዶ ሀገር ማፍረስ ደረጃ ከመድረሱ በፊት በትኩረት ሊሠራበት ይገባል” ደሴ ጥላሁን (ዶ.ር)