ዳሽን ቢራ ፋብሪካ በቡግና ወረዳ ለተቸገሩ ወገኖች 5 ሚሊዮን ብር ግምት ያለው የምግብ ድጋፍ አደረገ፡፡

59

ባሕር ዳር: ታኅሳስ 16/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ዳሽን ቢራ ፋብሪካ አክሲዮን ማኅበር በሰሜን ወሎ ዞን ቡግና ወረዳ ለተቸገሩ ወገኖች 5 ሚሊዮን ብር ግምት ያለው የምግብ ድጋፍ አድርጓል፡፡ የደብረ ብርሃን ዳሽን ቢራ ፋብሪካ ፕላንት ማናጀር ደረጀ ሙሉዓለም በሰሜን ወሎ ዞን ቡግና ወረዳ ለችግር ለተጋለጡ ወገኖች የዕለት ደራሽ ምግብ ፍጆታ የሚውል ድጋፍ ይዞ የሚሄድ የልዑካን ቡድን መሸኘታቸውን ገልጸዋል፡፡

በወረዳው ለችግር የተጋለጡ ወገኖች ይህን ወቅት አልፈው ጥሩ ጊዜ እንዲመጣላቸው መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል፡፡ የደብረ ብርሃን ዳሽን ቢራ ፋብሪካ የማኅበረሰብ አገልግሎት ሥራ አስኪያጅ ጌታነህ ዝቄ አክሲዮን ማኅበሩ በሰሜን ወሎ ዞን ቡግና ወረዳ በምግብ እጥረት ለተቸገሩ ወገኖች የዕለት ምግብ የሚውል 5 ሚሊዮን ብር ግምት ያለው 8 መቶ ኩንታል ዱቄት ወደ ቦታው መሸኘታቸውን አመላክተዋል፡፡

ዳሽን ቢራ ፋብሪካ በማኅበረሰብ አገልግሎት ዘርፍ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን ከመተግበር ጎን ለጎን በተፈጥሮ እና በሰው ሠራሽ አደጋ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ድጋፍ በማድረግ የድርሻውን እንደሚወጣም ገልጸዋል፡፡ ከደብረ ብርሃን ከተማ ኮሙዩንኬሽን የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው ለቡግና ወረዳ ወገኖች የተላከው የምግብ ድጋፍ ፈጥኖ በመድረስ ማኅበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት ያደረገው ጥረት መኾኑን አስታውቀዋል፡፡

በቀጣይ የሥራ ኃላፊዎች በሚሰጡት አቅጣጫ መሠረት ተመሳሳይ ድጋፍ የማድረጉ ሥራ እንደሚቀጥልም አመላክተዋል፡፡

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየሰላም ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ለሀገራዊ ሰላም በትብብር እንደሚሠሩ ገለጹ፡፡
Next article“ብልጽግና ፓርቲ ለሕዝብ ቃል በገባው መሰረት በዘላቂ ሰላም ግንባታና አካታች ልማት ስኬቶችን አስመዝግቧል” ተመሥገን ጥሩነህ