በሰሜን ጎንደር ዞን ዳባት ወረዳ የተመረቁ የሚሊሻ አባላት ሕዝብን ሊያገለግሉ እንደሚገባ ተገለጸ።

49

ደባርቅ: ታኅሣሥ 16/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በሰሜን ጎንደር ዞን ዳባት ወረዳ በንድፈ ሃሳብ እና በተግባር የታገዘ ሥልጠና ሲከታተሉ የቆዩ የሚሊሻ አባላት ሥልጠናቸውን አጠናቅቀው ተመርቀዋል። በምረቃ መርሐ ግብሩ የመከላከያ ሠራዊት መሪዎችን ጨምሮ በየደረጃው ያሉ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል።

በምረቃ መርሐ ግብሩ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የሰሜን ጎንደር ዞን የጸጥታ ጉዳይ አባል ሜጄር ጄኔራል አማረ ገብሩ ሚሊሻ በሰላም ጊዜ አምራች፣ በጦርነት ጊዜ ደግሞ ታሪክ የሚሠራ ጀግና ነው ብለዋል። ይሄም የጀግንነት ታሪክ በተለያዩ የታሪክ አጋጣሚዎች የታየ ሐቅ እንደኾነ አስረድተዋል።

ሜጄር ጄኔራሉ አሁን ላይ መንግሥት በሕዝቡ ጥያቄ መሠረት የሰላም አማራጭን ያመቻቸ ሲኾን ከሰላም አማራጩ ባፈነገጡ የጽንፈኛ ቡድኑ አባላት ላይ ሕጋዊ ርምጃ እየወሰደ ነው ብለዋል። የሰሜን ጎንደር ዞን ዋና አሥተዳዳሪ ዲያቆን ሸጋው ውቤ በዞኑ ያለው የጽንፈኛ ቡድኑ እንቅስቃሴ የተለያዩ መሠረተ ልማቶችን ከማውደም እና ከማደናቀፍ ባለፈ ለአካባቢው ማኅበረሰብም የስጋት ምንጭ መኾኑን ገልጸዋል።

ዋና አሥተዳዳሪው በቀጣይም ተመራቂ የሚሊሻ አባላቱ ሕግን እና መመሪያን መሠረት አድርገው የአካባቢውን ሰላም እና ደኅንነት እንዲያስጠብቁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየግንባታ ፕሮጀክቶች በጥራት እና በታለመላቸው ጊዜ እንዲጠናቀቁ በቅንጅት ሊሠራ እንደሚገባ የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር ገለጸ።
Next articleፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ በጎርጎሬስያውያን የዘመን ቀመር የልደት በዓልን ለሚያከብሩ ወገኖች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ፡፡