በ148 የመስኖ ፕሮጀክቶች ከ48 ሺህ ሄክታር በላይ ማሳ እየለማ ነው።

10

ደብረ ማርቆስ: ታኅሣሥ 16/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ግንባታቸዉ የተጓተቱ ነባር የመስኖ ፕሮጀክቶችን አጠናቆ ወደ ሥራ ለማስገባት ጥረት እየተደረገ መኾኑን የምሥራቅ ጎጃም ዞን መስኖ እና ቆላማ አካባቢወች ልማት መምሪያ አስታውቋል፡፡ የበጋ መስኖ ስንዴ ልማትን ዉጤታማ ለማድረግ የዉኃ መሳቢያ ሞተር ፓምፓችን ለአርሶ አደሮች ለማሰራጨት እየተሠራ መኾኑንም መምሪያው ገልጿል።

በዞኑ ተገንብተዉ ወደ ሥራ የገቡ አነስተኛ እና መካከለኛ የመስኖ ፕሮጀክቶችን በማሥተዳደር ለልማት እንዲዉሉ እያደረገ መኾኑን የመምሪያው ተወካይ ኀላፊ ሸጋየ ገደፋው ገልጸዋል ። በዞኑ ግንባታቸው ተጀምረው ያልተጠናቀቁ 30 መካከለኛ እና አነስተኛ የመስኖ ፕሮጀክቶች መኖራቸውን የጠቆሙት ተወካይ ኀላፊው በተያዘው በጀት ዓመት ወደ ሥራ የገቡ ሰባት የመስኖ ፕሮጀክቶችን አጠናቆ ወደ ተግባር ለማስገባት ጥረት እየተደረገ ነው።

በዞኑ ለ14 አዳዲስ አነስተኛ የመስኖ ፕሮጀክቶች የዲዛይን ጥናት መሥራት መቻሉን የጠቆሙት ኀላፊው በዞኑ ከዚህ በፊት በተገነቡ 148 የመስኖ ፕሮጀክቶች ከ48 ሺህ ሄክታር በላይ ማሳ እየለማ መኾኑን ገልጸዋል ። የበጋ መስኖ ስንዴ ልማትን ዉጤታማ ለማድረግ 1 መቶ የሚኾኑ የዉኃ መሳቢያ ሞተር ፓምፖችን ለአርሶ አደሮች ለማሰራጨት እየተሠራ እንደኾነም ተናግረዋል፡፡

ከግንባታ ጥናት ጀምሮ አጋር ተቋማትን እና ማኅበረሰቡን በማሳተፍ ለመስኖ አዉታሮች ባለቤት በመስጠት ፍትሐዊ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ እየተሠራ መኾኑንም ተወካይ ኀለፊው ገልጸዋል፡፡

የተጀመሩ የመስኖ መሠረተ ልማቶችን በተቀመጠላቸው ጊዜ ሠርቶ ለማጠናቀቅ ማኅበረሰቡ ዘላቂ ሠላም እንዲሰፍን የድርሻቸውን እንዲወጡ ተወካይ ኀላፊው ጠይቀዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

Previous articleየሙቀት አማቂ ጋዞች ልቀትን 69 በመቶ ገደማ መቀነስ የሚያስችል ስምምነት ተፈረመ።
Next articleመጭው የጥምቀት በዓል ለንግዱ እንቅስቃሴ የሚኖረውን በጎ እድል በአግባቡ መጠቀም ይገባል።