
አዲስ አበባ: ታኅሣሥ 16/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ስምምነቱን የኢትዮጵያ የአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን ከሰባት የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች ጋር ነው የተፈራረመው። የኢትዮጵያ አካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ለሊሴ ነሜ ዜጎች በንፁህ አካባቢ የመኖር መብታቸው እንዲከበር እና የአየር ንበረት ለውጥ ተፅዕኖን ለመቀነስ አስፈላጊ ሥራዎች ይሠራሉ ብለዋል።
ስምምነቱ በኢትዮጵያ ብሔራዊ የሙቀት አማቂ ጋዞች ልቀትን ለመቆጣጠር የሚጠቅም መኾኑንም ገልጸዋል። ኢትዮጵያም እንደ ሀገር የሙቀት አማቂ ጋዞች ልቀትን 68 ነጥብ 8 በመቶ ለመቀነስ ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ቃል የገባች በመኾኑ ይህንን ለማሳካት ይጠቅማል ነው ያሉት። የውኃ እና ኢነርጅ ሚኒስትር ድኤታ ሱልጣን ወሊ የኢትዮጵያን የኀይል አቅርቦት ከከሰል እና ነዳጅ ወደ ታዳሽ ኀይል ሙሉ በሙሉ የማስገባት ሥራ አየተሠራ ነው ብለዋል።
ይህም የሙቀት አማቂ ጋዞች ልቀትን በማስወገድ ለአዎንታዊ የአየር ንብረት ለውጥ ሥራ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው አብራርተዋል። በስምምነቱ የትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ ሚኒስቴር፣ የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር፣ የከተማ እና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር፣ የግብርና ሚኒስቴር፣ የማዕድን ሚኒስቴር እና የደን ልማት አሥተዳደር በሥፍራው ተገኝተው የስምምነት ፊርማውን ፈርመዋል።
ዘጋቢ፡- አንዱዓለም መናን
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!