የሰላም ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሀገራዊ የሰላም ግንባታ ሥራዎች በጋራ እንደሚሠሩ ገለጹ።

31

ባሕር ዳር: ታኅሣሥ 15/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የሰላም ሚኒስትሩ መሐመድ እድሪስ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ጋር በመንበረ ፓትርያርክ ትውውቅ አድርገዋል። በትውውቁ በኢትዮጵያ የተጀመረውን ሰላም አጠናክሮ ለመቀጠል በሚቻልበት ሁኔታ የጋራ ምክክር አድርገዋል።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቤተክርስቲያኗ ከመንግሥት ጋር በመደጋገፍና በመቀራረብ ለሰላም ግንባታ እንደምትሠራ ተናግረዋል። የሰላም ሚኒስትሩ ለትውውቅና ለውይይት ወደ መንበረ ፓትሪያርክ በመምጣታቸውም አድንቀዋል።

የሰላም ሚኒስትሩ መሐመድ እድሪስ ቤተ ክርስቲያኗ በሰላምና በሀገረ መንግሥት ግንባታ ካላት የካበተና የዳበረ ልምድ በመነሳት የተጀመረው የሰላም ሂደት እንዲጎለብት፣ ለሰላም በዘላቂነት መፍትሔ እንዲመጣ የበኩሏን ሚና እንድትወጣ ጠይቀዋል።

ኢዜአ እንደዘገበው መንግሥት ሁልጊዜም ለሰላም የሚከፈል ዋጋን ለመክፍል ያለውን ቁርጠኝነትም ገልጸዋል።

የሰላም ሚኒስቴር ከሁሉም የሃይማኖት ተቋማት እና አባቶች ጋር በትብብርና በቅርበት እንደሚሠራም አረጋግጠዋል፡፡

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽኑ ለአማራ ሕዝብ ያመጣውን ዕድል አናባክነውም” በአማራ ክልል የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፖርቲዎች የጋራ ምክር ቤት
Next articleቴክኖሎጅን ለፍርድ ቤት ሥራ መጠቀም መጀመሩን የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አስታወቀ።