የአማራ ክልል መሪዎች የተለያዩ የግንባታ ሥራዎች እንቅስቃሴን እየተመለከቱ ነው።

30

ባሕር ዳር: ታኅሣሥ 15/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ከፍተኛ መሪዎች ዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን በባሕር ዳር ከተማ እያከናወናቸው ያሉ የግንባታ ሥራዎች ያሉበትን እንቅስቃሴ ተዘዋውረው ተመልክተዋል።

በምክትል ርእሰ መሥተዳደር ማዕረግ የከተማ ዘርፍ አሥተባባሪ እና የከተማ እና መሰረተ ልማት ቢሮ ኀላፊ አሕመዲን ሙሐመድ (ዶ.ር)፣ በምክትል ርእሰ መሥተዳደር ማዕረግ የማኅበራዊ ዘርፍ አሥተባባሪ እና የትምህርት ቢሮ ኀላፊ ሙሉነሽ ደሴ (ዶ.ር)፣ የአማራ ክልል ጤና ቢሮ ኀላፊ አብዱልከሪም መንግሥቱ፣ የገቢዎች ቢሮ ኀላፊ ክብረት ማሕሙድ እና ሌሎችም መሪዎች በምልከታው ላይ ተገኝተዋል።

መሪዎቹ እየተመለከቷቸው ከሚገኙት ፕሮጀክቶች ውስጥ የፈለገ ሕይወት አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የእናቶች እና ሕጻናት ሕክምና ክፍል ግንባታ፣ የገቢዎች ሚኒስቴር ባሕር ዳር ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ባለ ዘጠኝ ወለል ሕንፃ እና የቤዛዊት ሸኔል ሆም የሕንጻ ተገጣጣሚ አካል ማምረቻ ፋብሪካ ይገኙበታል።

የምልከታው ዋና አላማም በግንባታ ላይ የሚገኙት ፕሮጀክቶች በፍጥነት ተጠናቅቀው ወደ አገልግሎት እንዲገቡ ለማስቻል ነው።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleለእንስሳት ጤና ትኩረት መስጠት ለሁለንተናዊ የኅብረተሰብ ጤና ማሰብ ነው።
Next articleየወይዘሮ ስሂን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅን በቴክኖሎጅ ለማዘመን እየተሠራ ነው፡፡