አምባሳደር ምስጋኑ አረጋ ከሶማሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ድኤታ ጋር ተወያዩ።

36

ባሕር ዳር: ታኅሳስ 15/2017 ዓ.ም (አሚኮ)የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ድኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አረጋ ከሶማሊያ የውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር ድኤታ አሊ ሞሐመድ ኦማር ጋር ተወያይተዋል።

በውይይታቸው የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ማጠናከር እና የአንካራውን ስምምነት መተግበር በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ መክረዋል፡፡

በአፍሪካ ቀንድ ሰላምን ለማስፈን እና ብልጽግናን ለማረጋገጥ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነትን ማጠናከር እንደሚገባ የተናገሩት ሚኒስትር ድኤታዎቹ፤ ይህን ግንኙነት ለማጠናከር ስለመምከራቸው መግለጻቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበበጀት ዓመቱ 597 የመንገድ እና ድልድይ ፕሮጀክቶችን ለማጠናቀቅ እየተሠራ ነው፡፡
Next articleየጡረታ ሕጉ ምን ይላል?