በበጋ መስኖ ስንዴ 122 ሺህ ሄክታር መሬት በላይ መሸፈኑን የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ አስታወቀ።

38

ባሕር ዳር: ታኅሣሥ 15/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በበጋ መስኖ ስንዴ 122 ሺህ ሄክታር መሬት በላይ መሸፈኑን የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ አስታውቋል።

በአማራ ክልል ለበጋ የመስኖ ሥራ ልዩ ትኩረት ተሰጥቷል። በበጋ መስኖ ልዩ ትኩረት ከተሰጣቸው ልማቶች መካከል ስንዴ ከግንባር ቀደሞቹ ነው።

በአማራ ክልል በ2017 ዓ.ም በበጋ መስኖ ስንዴ እስካሁን 122 ሺህ 378 ሄክታር መሬት በዘር መሸነፉን ግብርና ቢሮው አመላክቷል።

በክልሉ በተያዘው ዓመት በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት ከ254 ሽህ ሄክታር በላይ መሬት በማልማት 9 ነጥብ 4 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ለማምረት ታቅዷል ነው የተባለው።

ከክልሉ ግብርና ቢሮ የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው የበጋ መስኖ ስንዴ በዘር የመሸፈን ሥራውን እስከ ታኅሣሥ 30 ድረስ የዕቅዱን አብዛኛውን ለማጠናቀቅ እርብርብ እየተደረገ ነው ተብሏል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleሚሊሻ የሰላም ዘብ እና የሕዝብ ጠባቂ ነው።
Next articleበበጀት ዓመቱ 597 የመንገድ እና ድልድይ ፕሮጀክቶችን ለማጠናቀቅ እየተሠራ ነው፡፡