
ወልድያ: ታኅሣሥ 14/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የተፈጥሮ ሃብት ሥራ የንቅናቄ ተግባር ከጥር 01/2017 ዓ.ም ጀምሮ እንደሚከናወን የሰሜን ወሎ ዞን ግብርና መምሪያ አስታውቋል።
የዞኑ ግብርና መምሪያ ኀላፊ ተገኘ አባተ በዚህ ዓመት በ676 ተፋሰሶች ከ29 ሺህ በላይ ሄክታር መሬት የተፈጥሮ ሃብት ሥራ ለማከናወን መታቀዱን ገልጸዋል። በየደረጃው አስፈላጊ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ማጠናቀቅ ተችሏልም ብለዋል። ኀላፊው አዲሱን የግብርና ኤክስቴሽን አደረጃጀት ሥራ ላይ በማዋል ፍተሻ የሚካሄድበት የሙከራ ተግባር ታኀሣሥ 14/2017 ዓ.ም በዞኑ ሁሉም ወረዳዎች ላይ መከናወኑን ነግረውናል።
ይህ የሙከራ ሥራ ጥር 01/2017 ጀምሮ ለአንድ ወር ለሚቆየው የንቅናቄ ተግባር ክፍተቶችን ለመለየት እና ለመሙላት ያግዛልም ተብሏል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!