መሪዎች በደብረ ብርሃን ከተማ የሚገነባውን ዘመናዊ የፍሳሽ ቆሻሻ ማጣሪያ ፕሮጀክት እየተመለከቱ ነው።

33

ደብረ ብርሃን:ታኅሣሥ 14/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ከፍተኛ መሪዎች ከ300 ሚሊዮን ብር በላይ በኾነ ወጭ እየተገነባ የሚገኘውን ዘመናዊ የፍሳሽ ቆሻሻ ማጣሪያ ፕሮጀክት የሥራ እንቅስቃሴ እየተመለከቱ ነው።

በምልከታው ላይ የክልል እና የከተማ አሥተዳደሩ የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል።

የአማራ ክልል ውኃ እና ኢነርጂ ቢሮ ኀላፊ ማማሩ አያሌው (ዶ.ር)፣ የደብረ ብርሃን ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ በድሉ ውብሸትን ጨምሮ የክልል እና የከተማ አሥተዳደር የሥራ ኀላፊዎች በተገኙበት ነዉ ጉብኝቱ እየተካሄደ የሚገኘው።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ልጆቻችን ወደ ትምህርት ገበታቸው ይመለሱ” የተማሪ ወላጆች
Next articleበኦሮሚያ ክልል ሆሮ ጉዱሩ ዞን ሕዝባዊ ሰልፍ ተካሄደ፡፡