
ደብረ ማርቆስ: ታኅሣሥ 12/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በደብረ ማርቆስ ከተማ አሥተዳደር የሃይማኖት አባቶች ሰላምን ለማምጣት ትኩረቱን ያደረገ የሰላም ኮንፈረንስ አካሂደዋል።
በሰላም ኮንፈረንሱ አሚኮ ያነጋገራቸው የደብረ ማርቆስ ከተማ የሃይማኖት አባቶች በአማራ ክልል የተከሰተው የሰላም መደፍረስ በንግግር እና በይቅርታ እንዲፈታ የበኩላቸውን እየተወጡ መኾናቸውን ተናግረዋል። የሃይማኖት አባቶቹ እንደየ እምነታቸው ሰላም እንዲመጣ ተከታዮቻቸውን እያስተማሩ እንደሚገኙም ገልጸዋል።
“የሰው ልጆች ንግግርም ይሁን ተግባር ሰላም ሊሆን እንደሚገባ” ያሳሰቡት የእምነት አባቶች ሁሉም ማኅበረሰብ እንደየእምነቱ የተከሰተውን የእርስ በእርስ ግጭት አልባት እንዲያገኝ የበኩሉን እንዲወጣም ጥሪ አቅርበዋል።።
በክልሉ የተከሰተው ግጭት ካስከተለው ሰብዓዊ ጉዳት ባሻገር ዛሬም ድረስ ዜጎች በሰላም ወጥተው እንዳይገቡ ሠርተው እንዳይበሉ እንቅፋት ኾኗል ነው ያሉት። መንግሥት እና ታጥቀው የሚንቀሳቀሱ ኃይሎች ለሕዝባቸው ሲሉ ለንግግር እና ለይቅርታ ቁርጠኛ ሊሆኑ ይገባልም ብለዋል።
የሃይማኖት አባቶች በደብረ ማርቆስ ከተማ ባካሄዱት የሰላም ኮንፈረንስ በክልሉ የተከሰተውን የሰላም እጦት ለመፍታት በሚደረገው ጥረት ላይ ሊወጡት ስለሚገባ ኀላፊነት ትኩረት አድርገው መክረዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!በደብረደ