
ባሕር ዳር: ታኅሣሥ 12/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በአማራ ክልል በ2016/17 መኸር የምርት ዘመን 5 ነጥብ 2 ሚሊዮን ሄክታር መሬት በዘር ተሸፍኗል። 169 ሚሊዮን ኩንታል ምርትም ይጠበቃል።
በክልሉ እስካሁን ድረስ 4 ነጥብ 4 ሚሊዮን ሄክታር ሰብል ተሠብሥቧል። ይህም የዕቅዱን 85 በመቶ ይሸፍናል።
በቀሪ ቀናት በዘር የተሸፈነ ሰብል ሙሉ በሙሉ በመሠብሠብ አርሶ አደሩ መስኖ ልማት ላይ እንዲረባረብ እየተሠራ እንደኾነም ነው የተገለጸው።
ቀሪ ያልተሠበሠበ ሰብል መሠብሠብ፣ የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት፣ የተፈጥሮ ሃብት ልማት ጥበቃ ሥራ የቅድመ ዝግጅት ተግባራት እንዲጠናቀቁ እና ሌሎችም ሥራዎች እንዲሳለጡ በየደረጃው ያለ የግብርና መሪ ትኩረት ሰጥቶ እንዲሠራም የግብርና ቢሮ አሳስቧል።
ባለሙያዎችም ሙያዊ ድጋፍ የመስጠት ኀላፊነታቸውን እንዲወጡ ነው ጥሪ የቀረበው።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!