በአማራ ክልል የቱሪዝም ዐውደ ጥናት እየተካሄደ ነው።

35

ባሕር ዳር: ታኅሣሥ 12/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በአማራ ክልል ባሕል እና ቱሪዝም ቢሮ እና በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ትብብር የቱሪዝም ዐውደ ጥናት በባሕር ዳር እየተካሄደ ነው።

በዐውደ ጥናቱ ቅኝት የአማራ ክልል ወቅታዊ የቱሪዝም ኹኔታዎችን የመቋቋም ተቋማዊ አደረጃጀት እና የአጋር አካላት ሚና፣ የዘርፉ ተግዳሮቶች እና የወደፊት አቅጣጫዎች በሚሉ ጉዳዮች ዙሪያ ጥናታዊ ጽሑፎች ቀርበው ውይይት ይደረግባቸዋል ተብሎ ይጠበቃል።

በዐውደ ጥናቱ በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የከተሞች ልማት ዘርፍ አስተባባሪ እና የከተማ እና መሠረተ ልማት ቢሮ ኀላፊ አሕመዲን ሙሐመድ (ዶ.ር)፣ የክልል ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴዎች፣ የቢሮ ኀላፊዎች፣ የዩኒቨርሲቲ ምሁራን እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ መልዕክት፦
Next articleበአማራ ክልል እስካሁን ከ4 ሚሊዮን ሄክታር በላይ ሰብል ተሠብሥቧል።