የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ መልዕክት፦

41

የሰባት ሐይቆች መገኛዋ ቢሾፍቱ በተቀናጀ የኮሪደር ልማት ላይ ትገኛለች።

በከተማዋ የተጀመሩ የተፈጥሮ ጸጋን ወደ ጥቅም የሚቀይሩ የልማት እና የስማርት ሲቲ ተግባራት የሚበረታቱ እንዲሁም የቢሾፍቱን የሀገር ውስጥ እና የውጭ ቱሪስት መናገሻነት በከፍተኛ ሁኔታ የሚያሳድጉ ናቸው።

የተቀናጀ የኮሪደር ልማት ሥራዎቹ የከተማዋን ገፅታ፣ ዘመናዊነትና የነዋሪዎቿን ኑሮ የሚያሻሽሉ ናቸው፡፡እነዚህ የልማት ስራዎች በከተማዋ አመራርና በፕሮጀክት ሠራተኞች የሌት ተቀን ትጋት በአጭር ጊዜ ተጠናቅቀው ለአገልግሎት እንደሚበቁ ሙሉ እምነት አለን።

መንግስት ከተሞች በአረንጓዴ ውበት እና በዘመናዊ የክትመት ስርዓት ተመራጭ የአገልግሎትና ምቹ የመኖሪያ ማዕከላት እንዲሆኑ የጀመረውን ሥራ አጠናክሮ ይቀጥላል፡፡

Previous articleከ160 ሺህ በላይ ዜጎች የውጭ ሀገር የሥራ ሥምሪት አድርገዋል፡፡
Next articleበአማራ ክልል የቱሪዝም ዐውደ ጥናት እየተካሄደ ነው።