ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች በባሕር ዳር ከተማ የልማት ሥራዎችን እየተመለከቱ ነው።

60

ባሕር ዳር: ታኅሳስ 11/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በጉብኝቱ ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ፣ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኀላፊ እና የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አደም ፋራህ፣ ምክትል ርእሰ መሥተዳድር አብዱ ሁሴን (ዶ.ር)፣ የአማራ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ይርጋ ሲሳይን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች ተገንተዋል።

ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎቹ በጣና ሐይቅ ዳር እየተገነባ የሚገኘውን የጣና ማሪናን ነው እየጎበኙ የሚገኙት። በባሕር ዳር ከተማ እየተሠሩ ያሉ የልማት ሥራዎችንም ይመለከታሉ። የባሕር ዳር የኮሪደር ልማት እና ሌሎች የልማት ሥራዎች የጉብኝቱ አካላል ናቸው።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleሰላምን የናፈቁ አንደበቶች፣ ግጭትን የጠሉ ልቦች፣ ለሰላም የተዘረጉ እጆች በጎዳናዎች ተመላልሰዋል።
Next articleየኦዲት ግኝት ያለባቸው ተቋማት እርምት እንዲወስዱ የመንግሥት ወጪ አሥተዳደር እና ቁጥጥር ቋሚ ኮሚቴ አሣሠበ፡፡