ለ30 ሺህ ወጣቶች የኮደርስ ኦንላይን ሥልጠና እየተሰጠ መኾኑን የክልሉ ሥራ እና ሥልጠና ቢሮ ገለጸ።

20

ባሕር ዳር: ታኅሣሥ 11/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የፌዴራል መንግሥት በሦሥት ዓመታት ለ5 ሚሊዮን ወጣቶች የኮደርስ ኦንላይን ሥልጠና ለመስጠት ወደ ሥራ ስለመግባቱ የክልሉ ሥራ እና ሥልጠና ቢሮ ምክትል ኅላፊ አማረ ዓለሙ ተናግረዋል፡፡ በአማራ ክልልም በሦሥት ዓመታት ከ760 ሺህ በላይ የሚኾኑ ወጣቶችን ለማሠልጠን ታቅዶ ወደ ሥራ መገባቱን ነው ምክትል ኅላፊው የገለጹት።

በ2017 ዓ.ም ደግሞ 192 ሺህ የሚጠጉ ወጣቶችን የሥልጠናው ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሠራ ስለመኾኑ አብራርተዋል። እስከ አሁንም ለ111 ሺህ ወጣቶች ግንዛቤ ተፈጥሯል ብለዋል። 30 ሺህ ወጣቶች እየሠለጠኑ እንደሚገኙም ነው የጠቆሙት። 19 ሺህ ወጣቶች ደግሞ የብቃት ማረጋገጫ አግኝተዋል ነው ያሉት። ሥልጠናው በሁሉም የክልል ተቋማት ተደራሽ እንደሚኾንም አስገንዝበዋል።

የሚሰጠው ሥልጠና የሥራ ዕድል ከመፍጠር ባለፈ በቀጣይ ሀገሪቱ ወደ የዲጅታላይዜሽን አሠራር ለመግባት ለምታደርገው ሥራ አጋዥ መኾኑንም ገልጸዋል። ሥልጠናውን መውሰድ ዓለም አቀፍ የሥራ መስኮች ላይ የመሳተፍ ዕድል የሚፈጥር በመኾኑ ወጣቶች ትኩረት እንዲሰጡ አሳስበዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየሃይማኖት ተቋማት ለዘላቂ ሰላም ባላቸው ሚና ላይ ያተኮረ የፓናል ውይይት በድሬዳዋ እየተካሄደ ነው።
Next articleሰላምን የናፈቁ አንደበቶች፣ ግጭትን የጠሉ ልቦች፣ ለሰላም የተዘረጉ እጆች በጎዳናዎች ተመላልሰዋል።