የሃይማኖት ተቋማት ለዘላቂ ሰላም ባላቸው ሚና ላይ ያተኮረ የፓናል ውይይት በድሬዳዋ እየተካሄደ ነው።

30

ባሕር ዳር: ታኅሳስ 11/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የሃይማኖት ተቋማት ለዘላቂ ሰላም ባላቸው ሚና ላይ ያተኮረ የፓናል ውይይት በድሬዳዋ እየተካሄደ መኾኑን ኢዜአ ዘግቧል። ፓናሉ ሃይማኖቶች ለሰላም፣ ለአንድነት፣ ለአብሮነት እና ለሀገር ግንባታ ያላቸው ሚና” በሚል መሪ መልዕክት ነው እየተካሄደ ያለው።

ውይይቱ የሃይማኖት ተቋማት ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን እያከናወኑት ያለውን ተግባር ለማጠናከር ያለመ ነው ተብሏል። በፓናል ውይይቱ ላይ የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የሥራ አስፈፃሚ አባላት፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ኡጋዞች እና አባ ገዳዎች ተሳታፊ ኾነዋል።

የድሬዳዋ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሐር እና የካቢኔ አባላት የውይይቱ ተካፋዮች ናቸው። ውይይቱ የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ከድሬዳዋ ከተማ አሥተዳደር የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጋር በመተባበር የተዘጋጀ ነው።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየልጆች ገጽ (ኪድስ ሞድ)
Next articleለ30 ሺህ ወጣቶች የኮደርስ ኦንላይን ሥልጠና እየተሰጠ መኾኑን የክልሉ ሥራ እና ሥልጠና ቢሮ ገለጸ።