
ባሕር ዳር: ታኅሳስ 11/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኀላፊ እና የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ ባሕር ዳር ገብተዋል።
ባሕር ዳር ደጅ አዝማች በላይ ዘለቀ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ምክትል ርእሰ መሥተዳድር አብዱ ሁሴን (ዶ.ር)፣ የአማራ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ይርጋ ሲሳይን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።
አቶ አደም ፋራህ በባሕር ዳር በሚኖራቸው ቆይታ ከአማራ ክልል ከፍተኛ መሪዎች ጋር በሰላም፣ በልማት እና በሌሎች ጉዳዮች ዙሪያ ይወያያሉ ተብሏል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!