
ዛሬ በኦሮሚያ ክልል ቢሾፍቱ ከተማ የብረት ኢንዱስትሪ መንደር የሚገኘውን ስቲሊ አር. ኤም. አይ ኃላ/የተ/የግ/ ማህበር (STEELY RMI P.L.C) የብረታብረት ማምረቻ ፋብሪካን ጎብኝተናል።
ፋብሪካው ዘመናዊ የዲጂታል አሠራርን እና የታዳሽ ኃይልን በመጠቀም ከዚህ ቀደም ይጣሉ የነበሩ የብረት ቁርጥራጮችን መልሶ ጥቅም ላይ እያዋለ ይገኛል፡፡ በዚህም ለተለያዩ የግንባታ ግብዓት የሚውሉ የብረታብረት ምርቶችን እያመረተ መሆኑ የሚደነቅ ነው።
የብረታብረት ፋብሪካው ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በመተካት ረገድ አበረታች ውጤቶች እያመጣ እንዳለም ተመልክተናል፡፡
መንግሥት የብድር፣ የመሠረተ ልማትና የአሠራር ምቹ ሁኔታዎችን በመፍጠር የግሉ ዘርፍ ለኢኮኖሚ ዕድገቱ ዋና አንቀሳቃሽ (ሞተር) እንዲሆን የጀመረውን ጥረት አጠናክሮ ይቀጥላል።