በኦሮሚያ ክልል ለሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን 320 ተወካዮች ተመረጡ።

36

አዲስ አበባ: ታኅሣሥ 10/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በኦሮሚያ ክልል የሀገራዊ ምክክር መድረክ እየተካሄደ ነው።

በምክክር መድረኩ የአጀንዳ ማሠባሠብ ሥራን ለማከናወን ከ7 ሺህ በላይ የማኅበረሰብ ክፍሎች ተወካዮች ውስጥ 320 ተወካዮች ዛሬ ተመርጠዋል።

እነዚህ የተመረጡ የኅብረተሰብ ተወካዮች ታኅሣሥ 13/2017 ዓ.ም ጀምሮ የባለድርሻ አካላት የምክክር እና የአጀንዳ ማሠባሠብ ሥራ ላይ እንደሚሳተፉ ነው የተገለጸው።

የምክክር እና የአጀንዳ ማሠባሠብ ሥራውም ለአምስት ተከታታይ ቀናት እንደሚቀጥል የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አብራርቷል።

ዘጋቢ፦ ሽመልስ ዳኜ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleፍትሐዊ እና ሚዛናዊ አሠራርን በመከተል ሙስናን መታገል ይገባል፡፡
Next articleበበጀት ዓመቱ የታቀደውን የሥራ ዕድል ፈጠራ ለማሳካት እየሠራ መኾኑን የሥራ እና ሥልጠና ቢሮ አስታወቀ።