የውጭ ባንኮች ወደ ኢትዮጵያ እንዲገቡ መፈቀዱ አዲስ ምዕራፍ እንደኾነ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ገለጸ፡፡

43

ባሕር ዳር: ታኅሣሥ 10/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የውጭ ባንኮች ወደ ኢትዮጵያ እንዲገቡ መፈቀዱ ለኢትዮጵያ አዲስ ምዕራፍ ነው ሲሉ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ፕሬስ ሴክሬታሪያት ኀላፊ ቢልለኔ ስዩም ገልጸዋል።

ኀላፊዋ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባጋሩት ጹሑፍ እየተከናወነ ያለው የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ማሻሻያ እና ሊበራላይዜሽን በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) አመራር ሰጭነት እየተሠራ ያለ ተግባር መኾኑን ተናግረዋል።

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የባንክ ዘርፍ ለውጭ ኢንቨስትመንት ክፍት እንዲኾን የሚያስችለውን አዋጅ ማጽደቁ በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ አዲስ ምዕራፍ እንደሚኾነም ነው ያብራሩት፡፡

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleተስፋ ያለው የፍራፍሬ ልማት በደቡብ ወሎ
Next articleፍትሐዊ እና ሚዛናዊ አሠራርን በመከተል ሙስናን መታገል ይገባል፡፡