“ከጦርነት ያተረፍነው ሞት እና ውድመት ነው” የወግዲ ወረዳ ነዋሪዎች

42

ደሴ: ታኅሣሥ 09/2017 ዓ.ም (አሚኮ) “ከጦርነት እና ግጭት ሞት እና ውድመት እንጅ ያገኙት ጥቅም እንደሌለ በደቡብ ወሎ ዞን የወግዲ ወረዳ ነዋሪዎች ባካሄዱት ሰላማዊ ሰልፍ ገልጸዋል።

በክልሉ ሰላም እንዲሰፍን እና የሕግ የበላይነት እንዲረጋገጥ ነው ሰላማዊ ሰልፈኞቹ የተናገሩት።

የጸጥታውን ችግር እና እያስከተለ ያለውን ሁለንተናዊ ጉዳት ሕዝቡ በተገቢው መንገድ በድጋፍ ሰልፉ ገልጿልም ብለዋል።

በክልሉ የተፈጠረው ችግር በሕዝቡ ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ተጽዕኖ ከመፍጠሩ ባሻገር የሰብዓዊ ጉዳትንም አስከትሏል ነው ያሉት ሰልፈኞቹ።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ሕዝባችን የፅንፈኛን ድርጊትና ሃሳብ በአደባባይ ማውገዙን ከልብ እናመሠግናለን፤ የሰጠውን የሰላም ጥሪም ከልብ እናዳምጣለን፤ ዛሬም ለሰላም እና ስለሰላም እጆቻችንን እንዘረጋለን” አቶ ይርጋ ሲሳይ
Next article“ሕዝቡ የደገፈው ሰላምን ነው” ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ