
ጎንደር: ታኅሣሥ 09/2017 ዓ.ም (አሚኮ) “ለሰላም ዘብ እቆማለሁ” በሚል መሪ መልዕክት በጎንደር ከተማ በተካሄደው ሕዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ ነዋሪዎች ዘላቂ ሰላም እንዲመጣ የሚጠይቁ ድምጾችን አሰምተዋል።
ሀሃሳባቸውን ለአሚኮ የሰጡ ሰልፈኞች የሰላም እጦቱ የኑሮ ውድነትን በማባባስ፣ ሰላማዊ የሥራ እንቅስቃሴ እንዳይኖር አድርጓል ብለዋል።
የሰላሙ እጦቱ ዜጎች በሁለንተናዊ የእለት ከእለት እንቅስቃሴያቸው ላይ ሰፊ ችግር እንደፈጠረ ገልጸዋል። በዚህም ምክንያት የእለት ጉርስ ያጡ ዜጎች አሉ የሚሉት ነዋሪዎቹ አሁንም የሰላም ጥሪውን አጠናክሮ መቀጠል ይገባል ብለዋል።
በተለያየ የትምህርት ደረጃ ከሚማሩ ተማሪዎች መካከል ሃሳባቸውን የሰጡ ተማሪዎች በበኩላቸው ሰላም ባለመኖሩ ትምህርታቸውን በአግባቡ ለመማር መቸገራቸውን ነግረውናል።
ጥይት በተተኮሰ ቁጥር ተማሪ ተረጋግቶ ለመማር እና ውጤታማ ለመኾን አስቸጋሪ ነው ብለዋል። ዘላቂ መፍትሄው ሰላም መፍጠር ነው የሚል ሃሳብ ያላቸው ተማሪዎቹ ሁሉም አካል ሰላም እንዲመጣ እንዲያደርግ ጠይቀዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!