የእነብሴ ሳር ምድር ወረዳ እና የመርጡለ ማርያም ከተማ አሥተዳደር በጋራ ሕዝባዊ የድጋፋ ሰልፍ አካሄዱ።

21

ባሕር ዳር፡ ታኅሣሥ 09/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በምስራቅ ጎጃም ዞን የእነብሴ ሳር ምድር ወረዳ እና የመርጡለ ማርያም ከተማ አሥተዳደር በጋራ በመሆን ሰላም ለሁሉም ሁሉም ለሰላም በሚል መሪ መልእክት ሕዝባዊ የድጋፋ ሰልፋ አካሂደዋል። በድጋፍ ሰልፉ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የመንግሥት ሠራተኞች ፣የከተማ ነዋሪዎች ፣አርሶ አደሮች ፣ተማሪዎችና ሌሎች የኅብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል።

የሰልፉ ተሳታፊዎችም ካስተላለፏቸው መልእክቶች መካከል፦
.
👉 መንግሥት ያደረገውን የሰላም ጥሪ እንደግፋለን!
👉ለክልላችን የሚያስፈልገው ጦርነት ሳይሆን ሰላምና ልማት ነው!
👉 ሰላም የጋራ ሃብት ነው!
👉 መንግሥት ሕግ በማስከበር የዜጎችን ሰላም እና ደኅንነት ሊያሰከብር ይገባል!
👉 ለመከላከያ ሠራዊቱና ለክልላችን የጸጥታ ኀይሎች ዋጋና ክብር እንሰጣለን!
የሚሉትና ሌሎች መልዕክቶች ተላልፈዋል።

የሰልፉን አላማ በተመለከተ የመርጡለ ማሪያም ከተማ አሥተዳደር ምክትል ከንቲባ ብርሃኑ ዋለ መልዕክት አስተላልፈዋል።

መረጃው የእነብሴ ሳር ምድር ወረዳ ኮሙዩኒኬሽን ነው።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleማኅበረሰቡ በሰላም ወጥቶ እንዲገባና ሰላም እንዲሰፍን ሁሉም ኀላፊነቱን ሊወጣ ይገባል።
Next articleዘላቂ ሰላም እንዲመጣ የጎንደር ከተማ ነዋሪዎች ጠየቁ።