
ባሕር ዳር፡ ታኅሣሥ 09/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በምስራቅ ጎጃም ዞን በሞጣ ከተማ አሥተዳደር የሞጣ ከተማ እና የሁለት እጁ እነሴ ወረዳ ነዋሪዎች “ጦርነት ይብቃ” በሚል መሪ መልእክት ሕዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ ተካሂዷል።
“ሰላም በጋራ ይለማል በጋራ ይጠበቃል፣ ሰላም መተኪያ የሌለው ሃብት ነው፣ ጦርነት ይብቃ! መንግሥት ሕግ በማስከበር የዜጎችን ሰላም እና ደህንነት ሊያስጠብቅ ይገባል! የሚሉ መፎክሮች በሰልፉ ላይ ተስተጋብተዋል።
ማኅበረሰቡ በሰላም ወጥቶ እንዲገባና ልማትና ሰላም እንዲሰፍን ሁሉም ኀላፊነቱን ሊወጣ ይገባል ሲሉ በሰላማዊ ሰልፉ መልዕክታቸውን ያስተላለፉት የከተማ አሥተዳደሩ ከንቲባ ፀሃይ ወንድም “ችግሮቻችንን በመደማመጥ መፍታት እንጅ ልማትና ሰላምን በማደናቀፍ አይሆንም፤ ፋኖነትም ይህን ሊገልፅ አይችልም” ብለዋል።
ከንቲባው አያይዘውም ሰልፉ እንዲካሄድ አስተዋፅኦ ላበረከቱ አካላትና ለማኅበረሰቡም ምሥጋና አቅርበዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!