
እንጅባራ: ታኅሣሥ 09/2017 ዓም (አሚኮ) በሰልፉ የሃይማኖት አባቶች፣ ፈረሰኞች፣ ተማሪዎች እና ልዩ ልዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል።
የባንጃ ወረዳ ኮሙዩኒኬሽን ጽሕፈት ቤት እንደዘገበው መንግሥት በተደጋጋሚ የሚያቀርበውን የሰላም ጥሪ እንደግፋለን!!
ለክልላችን የሚያስፈልገው ጦርነት ሳይኾን ሰላም እና ልማት ነው!!
መንግስት ለሰላም መስፍን የሚወስዳቸውን ርምጃዎች እንደግፋለን!!
ሠላም የጋራ ሃብት ነው! በጋራ ይጠበቃል!!
ሰላም ከሌለ መማር የለም!
እኛ ተማሪዎች እስክርቢቶ እና ደብተር እንጂ የጥይት ድምፅ መስማት አንፈልግም!! የሚሉ መልዕክቶችም በሰልፉ ተላልፈዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!