
ወልድያ: ታኅሣሥ 09/2017 ዓ.ም (አሚኮ) “ሰላም ለሁሉም ሁሉም ለሰላም” በሚል መሪ መልዕክት የመንግሥት ሠራተኞች፣ ወጣቶች፣ ሴቶች እና ልዩ ልዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች የተሳተፉበት ሕዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ በወልድያ ከተማ ተካሂዷል።
የወልድያ ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ዱባለ አብራሬ የወልድያ ከተማ ሕዝብ በሰሜኑ ጦርነት መፈናቀልን፣ መሳደድን፣ መቸገርን አስተናግዶ አልፏል በመኾኑም የጦርነት አስከፊነት የቅርብ ጊዜ ትዝታው እንደኾነ ገልጸዋል።
ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባው ሁሉም ጦርነት በቃ ብሎ ሰላምን ከልቡ ሊሻ እንደሚገባም ነው ያስገነዘቡት፡፡
ጦርነት ትርፉ ሰብዓዊ እና ቁሳዊ ውድመት በመኾኑ ከመገዳደል በመውጣት ችግሮች በጋራ የሚፈቱበትን መንገድ መፈለግ ይገባል ብለዋል።
ወልድያን የተሻለች ለማድረግ ከተማ አሥተዳደሩ እየሠራ በመኾኑ ሕዝቡ ሁለንተናዊ ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል።
የአማራ ክልል ሥራ እና ሥልጠና በምክትል ቢሮ ደረጃ የሕዝብ ግንኙነት ኀላፊ አንዳርጋቸው ጎፋ የተሳሳተ መንገድ መዳረሻው የተሳሳተ ነው፤ እርስ በእርስ መጠፋፋትም ይበቃል ብለዋል፡፡
የአማራ ክልልን ሕዝብ የማይመጥን ግጭት ይበቃ ዘንድ ሕዝቡ አጥብቆ እንዲጠይቅም አሳስበዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!