
ባሕር ዳር: ታኅሳስ 9/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በአማራ ክልል በተለየዩ ከተሞች የተካሄደው ሕዝባዊ ሰልፍ በስኬት መጠናቀቁን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡
የክልሉ ፖሊስ ባወጣው መግለጫ የአማራ ክልል ሕዝብ ለዓመታት የተደቀነበትን የሰቆቃ ቀንበር የሚያወግዝ ሰላማዊ ሰልፍ “ሰላም ለሁሉም፤ ሁሉም ለሰላም” በሚል መሪ ሃሳብ በተለያዩ ከተሞች ማካሄዱን አንስቷል፡፡
ለዓመታት ክልሉ በጽንፈኛ ኃይሎች ምክንያት በሰቆቃ ሕይዎት ውስጥ እንዲጓዝ፣ እንዲዘረፍ፣ እንዲፈናቀል እና እንዲሰደድ መደረጉን ጠቁሟል፡፡
ይህን የመከራ ቀንበር የተሸከመው የክልሉ ሕዝብ የሰላም ካውንስል እስከመወከል የደረሰ “ሰላሜን መልሱልኝ” ጥያቄውን ከጀመረ መሰነባበቱን ጠቅሷል፡፡
ይሁን እንጂ ጽንፈኛው ኃይል የማኅበረሰብን የሰላም ጥያቄ “ጆሮ ዳባ ልበስ…” በማለት ከሰብል ማቃጠል ጅምሮ የክልሉን ሕዝብ ባሕል እና ወግ የማይገልጽ፣ ዘመኑን የማይመጥን እና ጸያፍ ተግባር መፈጸሙንም አስታውሷል፡፡
ዛሬ ከማለዳ ጀምሮ የጽንፈኛውን ተግባራት የሚያወግዝ ሰልፍ በተለያዩ የክልሉ ከተሞች ተካሂዶ በስኬት መጠናቀቁን ፖሊስ አስታውቋል፡፡
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!