
ባሕር ዳር: ታኅሣሥ 09/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመሥገን ጥሩነህ በአማራ ክልል እየተካሄዱ የሚገኙ ሕዝባዊ የሰላም ሰልፎችን አስመልክተው በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ የሚከተለውን መልእክት አስተላልፈዋል።
ዛሬ በተለያዩ የአማራ ክልል ከተሞች፣ የገጠር ወረዳዎች እና ቀበሌዎች ሕዝባችን ”ሰላም ለሁሉም፣ ሁሉም ለሰላም” በሚል መሪ ሃሳብ በነቂስ ወጥቶ ላሳየው የሰላም የድጋፍ ሰልፍ ምስጋና ይገባዋል።
ሰላም ወዳዱ ሕዝባችን መንግሥት ለሰላም እያቀረበ ያለውን ተደጋጋሚ ጥሪ በመደገፍ እና ጽንፈኝነትን በማውገዝ የታጠቁ ቡድኖች ወደ ሰላም እንዲመጡ ጥሪ አቅርቧል። በመኾኑም የአማራ ክልልን የሰላም እና የልማት ማዕከል ለማድረግ ሁሉም ለሰላም ዘብ ሊቆም ይገባል።
መንግሥት ሁልጊዜም ቢኾን ለሰላም በሩ ክፍት በመኾኑ ትጥቅ ያነሱ ቡድኖች ጽንፈኝነት እና ግጭት ማንንም እንደማይጠቅም በመገንዘብ ወደ ሰላማዊ መድረኩ እንዲመጡ ጥሪ እናቀርባለን።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!