በአየሁ ጓጉሳ ወረዳ መንግሥት እየወሰደ ያለውን ሕግ የማስከበር እርምጃ የሚደግፍ ሕዝባዊ ሰልፍ ተካሂዷል።

16

እንጂባራ: ታኅሣሥ 09/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በአዊ ብሔረሰብ አሥተዳደር አየሁ ጓጉሳ ወረዳ መንግሥት እየወሰደ ያለውን ሕግ የማስከበር እርምጃ የሚደግፍ ሕዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ ተካሂዷል።

በሕዝባዊ ሰላማዊ ሰልፉ የተገኙ ነዋሪዎች መንግሥት በተደጋጋሚ የሚያቀርበውን የሠላም ጥሪ እንደግፋለን ብለዋል። ለክልሉ የሚያስፈልገው ጦርነት ሳይኾን ሠላም እና ልማት መኾኑን ተናግረዋል።

መንግሥት ለሰላም መስፍን የሚወስዳቸውን እርምጃዎች እንደሚደግፉም ገልጸዋል። ሠላም የጋራ ሀብት ነው በጋራ ይጠበቃል፣ ሠላም ከሌለ መማር የለም ብለዋል።

ጽንፈኛው ኃይል በንጹሐን ላይ የሚያደርሰውን ግፍ በደል፣ ጭፍጨፋ፣ ዝርፊያ በጽኑ እናወግዛለን ነው ያሉት።

በሰልፉ የተገኙ ተማሪዎች እኛ ተማሪዎች እስክርቢቶ እና ደብተር እንጂ የጥይት ድምጽ መስማት አንፈልግም ብለዋል። ከአየሁ ጓጉሳ ወረዳ ኮምዩኒኬሽን የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው ጽንፈኛው ኃይል በፈረስ ቤት ደጋ ዳሞት በንጹሐን ላይ ያደረሰውን ጅምላ ግድያ በጽኑ እንደሚያወግዙ ገልጸዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ክልላችን የሰላም እና የልማት ማዕከል ለማድረግ ሁላችንም ለሰላም ዘብ እንቆማለን” የምዕራብ ደምቢያ ወረዳ ነዋሪዎች።
Next article“መንግሥት ሁልጊዜም ቢኾን ለሰላም በሩ ክፍት ነው፤ ትጥቅ ያነሱ ቡድኖች አሁንም ቢኾን ወደ ሰላማዊ መድረኩ እንዲመጡ ጥሪ እናቀርባለን” ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመሥገን ጥሩነህ