በከሚሴ ከተማ መንግሥት በተደጋጋሚ የሚያደርገውን የሰላም ጥሪ የሚደግፍ ሰላማዊ ሰልፍ ተካሄደ።

19

ከሚሴ: ታኅሣሥ 09/2017 ዓ.ም (አሚኮ)

በኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር ከከሚሴ ከተማ እና ከደዋ ጨፋ ወረዳ የተውጣጡ የኅብረተሰብ ክፍሎች ጽንፈኛ ቡድኖች እያደረሱ ያለውን ጉዳት እንደሚያወግዙ በሰላማዊ ሰልፍ ገልጸዋል።

ሕዝቡ በሰላም ወጥቶ እንዲገባ፣ ልጆች እንዲማሩ እና የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ ያለስጋት ለመከወን ታጥቀው የሚንቀሳቀሱ አካላት ወደ ሰላም እንዲመጡ ሰልፈኞቹ ጥሪ አቅርበዋል።

ሕዝባዊ ሰላማዊ ሰልፈኞች እንዳሉት ጽንፈኛ ኀይሎች በንፁሃን ላይ የሚፈጽሙት ግድያ፣ ማንገላታት እና ማፈናቀል ሊቆም ይገባል ነው ያሉት።

ሰላም የጋራ ሃብት እንደኾነም አስገንዝበዋል። ሕጻናትን ከትምህርት ገበታቸው ማስቀረት ተገቢ እንዳልኾነም ሰልፈኞቹ ተናግረዋል።

ዘጋቢ፦ ይማም ኢብራሂም

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየቅድስት ሥላሴ ካቴድራል እድሳት ተጠናቅቆ ጥር 6/2017 ዓ.ም ይመረቃል።
Next articleማንኛውም ችግር በሰላማዊ መንገድ ሊፈታ እንደሚገባ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ በድሉ ውብሸት ተናገሩ።