በምዕራብ ጎንደር ዞን ምዕራብ አርማጭሆ ወረዳ ሕዝባዊ ሰላማዊ ሠልፍ እየተካሄደ ነው።

15

በሰልፉም መንግሥት በተደጋጋሚ የሚያደርገውን የሰላም ጥሪ እንደግፋለን! በደምበጫ በገርጨጭ፣ በላሊበላና በሌሎች አካባቢዎች ንፁሃንን የጨፈጨፉ ፅንፈኛ ኀይሎች ለሕግ ይቅረቡልን! ክልላችንን የሰላምና የልማት ማዕከል ለማድረግ ሁላችንም ለሰላም ዘብ እንቆማለን!

መንግሥት ሕግ በማስከበር የንፁሃን ሰዎችን ገዳዮች ለሕግ ያቅርብልን!

መንግሥት ለሰላም መስፈን የሚወስዳቸውን እርምጃዎች እንደግፋለን!

በደጋ ዳሞት ፈረስ ቤት ከተማ ፅንፈኛው ኀይል በንፁኀን ላይ የፈፀመውን ዘግናኝ ጭፍጨፋና ግድያ በፅኑ እናወግዛለን!

ንፁኀንን በግፍ እየገደሉ በአስከሬናቸው መነገድ አረመኔያዊነት ነው!

የልማት ማዕከል የነበረውን ክልላችንን የጦርነት ቀጠና ለማድረግ የሚሠራው ሥራ የባንዳነትና የፅንፈኝነት ጥግ ነው!

ንፁኀንን በግፍ መጨፍጨፍ የአረመኔነት ጥግ ስለሆነ ሊወገዝ ይገባዋል!

ለክልላችን የሚያስፈልገው ጦርነት ሳይሆን ሰላም እና ልማት ነው!

ፅንፈኛ እና ተላላኪዎች ከባዕዳን ተልዕኮ ወጥተው የሰላምን አማራጭ ሊከተሉ ይገባል!

ሰላም የጋራ ሀብት ነው፤ በጋራ ይለማል በጋራ ይጠበቃል!

መንግሥት ሕግ በማስከበር የዜጎችን ሰላምና ደኅንነት ሊያስጠብቅ ይገባል!

ፅንፈኛው ኀይል በንፁሃን ላይ የሚፈፅመው ግድያ፣ ማገትና ማፈናቀል ሊቆም ይገባል!

መከላከያ ሠራዊታችን፣ የፌዴራል የፀጥታ ኀይሎች እና የክልላችን የፀጥታ ኀይሎች ለከፈሉት ዋጋ ክብር እንሰጣለን! የሚሉ መልዕክቶች ተስተጋብተዋል።

Previous articleልጆቻቸው ያለችግር እንዲማሩ መንግሥት ሕግ ማስከበሩን አጠናክሮ እንዲቀጥል የዱር ቤቴ ከተማ ነዋሪዎች ባካሄዱት ሰላማዊ ሰልፍ ገለጹ።
Next articleበስማዳ ወረዳ እና በወገዳ ከተማ የሕግ ማስከበር ሥራዎችን የሚደግፍ ሕዝባዊ ሰልፍ ተካሄደ።